የቢንጌት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ተኛ መደበኛ እና 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ

By BINGET Microfinance

2017 EC

የቢንጌት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ተኛ መደበኛ እና 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 366(1)፣ 367 (1 እና 2)፣ 370፣ 371፣ 372 እና 393 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 13(1 እና 3)፣ 18(3)፣ 20(1) እና 21(1) ድንጋጌዎች መሰረት ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ አድራሻው ከዚህ በታች በተዘረዘረው የማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል። ስለሆነም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን ሰዓት እና ቦታ ተገኝታችሁ በጉባኤው ላይ እንድትሳተፉ የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን በአክብሮት ያቀርባል። ባለአክሲዮኖች በጉባኤው ለመገኘት ኢትዮጵያዊነታችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ፤ መንጃ ፈቃድ፣ ፓስፖርት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነታችውን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ዋናውን ከፎቶ ኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል፣ በውክልና የሚገኙ ከሆነ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆኑን የሚያረጋግጥ የታደስ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዘው መገኘት ይኖርባቸዋል። በጉባኤዉ ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 አንቀጽ 377(1) ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስብሰባዉ እስከሚካሄድበት ከላይ በተጠቀሰው የማህበሩ ዋና መ/ቤት ቀርበዉ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀዉን የውክልና መስጫ ቅጽ በመሙላት ተወካያቸው ተገኝተው ድምጽ እንዲሰጡ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በሰነዶች ማርጋገጫና ምዝገባ ኤጅንሲ ወይም አግባብ ባለው አካል በተሰጠ ውክልና በስብሰባ ላይ የሚገኙ ተወካይ የወካዩን ባለአክሲዮን ኢትዮጵያዊነት ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊነት የሚያረጋግጥ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውን ከኮፒ ጋር ይዞው መገኘት ይኖርባቸዋል፡

የቢንጌት አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 4ተኛ መደበኛ እና 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ